ከባድ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አየር ማረፊያ ከጦርነቱ ማብቃት ከዓመት በኋላ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
ከባድ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አየር ማረፊያ ከጦርነቱ ማብቃት ከዓመት በኋላ

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ዋነኛ ተቋማት መካከል የታሪካዊቷ ከተማ የአክሱም አየር ማረፍያ አንዱ ነው።

ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለአክሱም አውሮፕላን ማረፍያ ጥገና 200 ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታውቆ ነበር።

ቢሆንም እስካሁን ጥገናው አልተጀመረም። አየር መንገዱ በረራ ባለመጀመሩ ከተማዋ ከፍተኛ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ውስጥ መግባቷን የከተማዋ ከንቲባ እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።