ከ200 በላይ ሰዎች ሞት ምክንያት ስለሆነው የእምነት ቡድን መሪ የወንድሙ ምስክርነት
ከ200 በላይ ሰዎች ሞት ምክንያት ስለሆነው የእምነት ቡድን መሪ የወንድሙ ምስክርነት
አስካሁን በተደረገው ፍለጋ ከሁለት መቶ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል የተባለው የእምነት ቡድን መሪ ፓስተር ፖል ማኬንዚ ዋነኛ ተጠያቂ ሆኖ በእስር ላይ ይገኛል።
የቡድኑ መሪ ተከታዮቹን እስከ ሞት በሚያደርስ ሁኔታ እራሳቸውን እንዲያስርቡ አስገድዷል ተብሎ ቢከሰስም እሱ ግን ይህንን ያስተባብላል።
የኬንያዊው ፓስተር ማኬንዚ ወንድም የተከሰተውን ነገር ለመቀበል እንደተቸገረ እና “ወንድሜ መልካም ሰው ነበር” ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።
ፓስተር ፖል ማኬንዚ ይሰብክ ከነበረው የምጽዓት ቀን መቃረብ ጋር በተያያዘ እስካሁን ከ600 በላይ ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ተናግሯል።



