የአካል ጉዳት ሕልሟን ከማሳካት ያላገዳት ወጣቷ የሕክምና ዶክተር

የአካል ጉዳት ሕልሟን ከማሳካት ያላገዳት ወጣቷ የሕክምና ዶክተር

ዶክተር ዕድላዊት አበባው በተፈጥሮ አንድ እጇ ላይ የአካል ጉዳት አለባት። ይህ የአካል ጉዳት ግን በልጅነቷ ያለመቻቸውን ግቦች ከማሳካት አላገዳትም።

ቤተሰቦቿ በሕክምና ሙያ ላይ የተሰማሩ በመናቸው የእርሷም ሕልም የነበረው በትምህርቷ በርትታ የተዋጣላት ሐኪም በመሆን ነበር።

በመሆኑም ዶክተር ዕድላዊት ሁኔታዎች ሳይገድቧት የሕክምና ትምህርቷን አጠናቃ አሁን በሐረሚያ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና በተቋሙ ሥር በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ የቆዳ ሐኪም ነች።