ፀጋ በላቸው፡ “የመሰበር ምልክት መሆን አልፈልግም”
ፀጋ በላቸው፡ “የመሰበር ምልክት መሆን አልፈልግም”
በቀድሞው የፖሊስ አባል እና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጠባቂ ተጠልፋ ዘጠኝ ቀናትን ያሳለፈችው ፀጋ በላቸው ጉዳይ ከእገታው ነጻ ስትወጣ ያበቃ አልነበረም። ከጠላፊው ዋና ሳጅን የኋላመብራት ወልደማርያም የፍርድ ውሳኔ ጋር በተያያዘም በድጋሚ ጉዳዩ ትኩረት ስቦ ነበር። ካለፈው ዓመት ጀምሮ ደግሞ ፀጋ ከሀገር ተሰድዳለች።
ፀጋ፤ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ተጠልፋ ስላሳለፈቻቸው ቀናት፣ ነጻ ስለወጣችበት መንገድ እና ከሀገር ለመሰደድ ያበቃትን ምክንያት አስረድታለች። “የመሰበር ምልክት መሆን አልፈልግም” የምትለው ፀጋ፤ ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም ተናግራለች።



