ካርበንዳይኦክሳይድ በአየር ንብረት ለውጥ ውስጥ ያለው ቁልፍ ሚና ምንድን ነው?
ካርበንዳይኦክሳይድ በአየር ንብረት ለውጥ ውስጥ ያለው ቁልፍ ሚና ምንድን ነው?
ምድር ያለካርበንዳይኦክሳይድ ለኑሮ የማትመች ቀዝቀዛ ትሆን ነበር። ካርቦንዳይኦክሳይድ ከፀሐይ የሚመጣን ሙቀት በከባቢ አየር ውስጥ በማስቀረት የምድርን ሙቀት እንዲመጣጠን ይረዳል።
ነገር ግን ከሚያስፈልገው በላይ መጠኑ ከመጨመሩ ደግሞ የምድራችን የሙቀት መጠን እንዲጨምር በማድረግ ከባድና ውስብስብ ችግርን ያስከትላል።
በተለያዩ የሰው ልጆች ተግባራትና እንቅስቃሴዎች አማካይነት ከፍተኛ መጠን ያለው በካይ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር እየገባ በመሆኑ የካርበንዳይኦክሳይድ መጠን እየጨመረ ነው። ይህም የምድርንና የሕዝቧን ደኅንነት አሳሳቢ አድርጎታል።
ይህ ቪዲዮ የካርበንዳይኦክሳይን ምንነት እና በዓለም የአየር ጸባይ ለውጥ ላይ የሚኖረውን ሚና ያብራራል።



