ኦሊምፒክ የኪነ ጥበብ ውድድሮች እንደነበሩት ያውቃሉ? የፓሪስ ኦሊምፒክ ከመቶ ዓመት በፊት እና በኋላ

የ1924 ኦሎምፒክ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ የፈረንሳይዋ ርዕሰ መዲና ፓሪስ ውድድሩን ካስተናገደች ከ100 ዓመታት በኋላ በድጋሚ የምታዘጋጀው ነው።

ከዚያ ጊዜ ወዲህ በፓሪስ ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል። በ1924ቱ ኦሊምፒክ ከሥነ ጥበብ እስከ አጭር ርቀት ውድድሮች ተከናውነዋል። አንዳንዶቹ ውድድሮች የመጀመሪያቸውም፣ የመጨረሻቸውም ነበር።

ከሦስት ሺህ በላይ ስፖርተኞች በ17 የስፖርት ዓይነቶች ተወዳድረዋል። ከመቶ ዓመት በኋላ የውድድር ዓይነቶቹ ቁጥር ተበራክቷል።

ፓሪስ ዘንድሮ በ32 ስፖርቶች 329 ሜዳሊያ ለመሸለም አዘጋጅታለች። ብዙዎቹ ውድድሮች ከኦሊምፒክ ውጪ ሆነዋል። አዳዲስ ስፖርቶች ደግሞ ተካተዋል። ክብረ ወሰኖች በተደጋጋሚ ተሰብረዋል። ቴክኖሎጂ እና መሠረተ ልማቶች በከፍተኛ ደረጃ አድገዋል።

የ1924 ኦሊምፒክ በፒየር ደ ኩበርቲን ሥር ለመጨረሻ ጊዜ የተከናወነ ውድድር ነበር። ኩበርቲን የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት እና በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ውድድሩን ያነቃቁ ሰው ነበሩ።

አሁን ፌዴሬሽኖች ውድድሩን በቁም ነገር መመልከት ጀምረዋል። የውድድር ሕግጋት ደረጃቸውን የጠበቁ ሆነዋል። በበርካታ አገራት የሚገኙ የኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ምርጥ ስፖርተኞቻቸው እንዲሳተፉ የማጣሪያ ውድድር ማዘጋጀት ጀምረዋል።

የ2024 ኦሊምፒክ ከቀደመው ውድድር በእጅጉ የተለየ ይሆናል። ፓሪስ 10 ሺህ 500 ስፖርተኞችን ተቀብላ ታስተናግዳለች።

የአውሮፓውያኑ 1924 መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ 19 ሺህ 052 ተመልካቾች በኦሊምፒክ ስታዲየም (ስታድ ዴ ኮሎምበስ) ተገኝተው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን ተከታትለዋል።

በሰሜን ምዕራብ ፓሪስ የሚገኘው ስታዲየም ለጨዋታው ታድሶ የነበረ ሲሆን የትራክ፣ የእግር ኳስ እና የራግቢ ውድድርም አስተናግዶ ነበር።

የ2024 ኦሊምፒክ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ብዙ የተለፋበት፣ አዝናኝ እና ልዩ በዓል እንዲሆን ሆኖ ተዘጋጅቷል።

ከሴይን ወንዝ 6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በፓሪስ በኩል ጀልባዎች ይጓዛሉ። እያንዳንዱ የኦሊምፒክ ቡድን የራሱ ጀልባ ይኖረው እና በከታማዋ ታዋቂ ምልክቶች በኩል ያልፋሉ።

ዝግጅቱ በዓለም ዙሪያ ወደ አንድ ቢሊዮን በሚጠጉ ሰዎች በቴሌቪዥን እንደሚታይ ይጠበቃል።

አንድ ክፍለ ዘመን ምን ዓይነት ለውጥ እንደሚፈጥር ያሳያል።

በ1924 ኦሊምፒክ በአጠቃላይ 625 ሺህ ተመልካቾች ዝግጅቱን ለመከታተል ተገኝተዋል። ዘንድሮ ደግሞ ከ15 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች ይጠበቃሉ።

የኦሊምፒክ የኪነ ጥበብ ውድድሮች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የኦሊምፒክ መጀመሪያዎች

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

የኦሊምፒክ መንደር

ለመጀመሪያ ጊዜ በ1924 ነበር ስፖርተኞች በኦሊምፒክ መንደር ውስጥ አብረው መቆየት የጀመሩት። በኦሊምፒክ ስታዲየም አቅራቢያ የተገነባው መንደር ፖስታ ቤት፣ የዜና ወኪል፣ የምንዛሪ ቢሮ፣ ፀጉር ቤቶች እና ሬስቶራንትን ያካተተ ነበር።

የሚዲያ ሽፋን

የ1924ቱ ውድድር በራዲዮ ቀጥታ ሥርጭት በማግኘት የመጀመሪያው ነበር። ውድድሩን ለመዘገብ ፈቃድ የተሰጣቸው 724 ጋዜጠኞች ነበሩ። አብዛኞቹ የውጭ አገር ጋዜጠኞች ነበሩ።

የኦሊምፒክ ቦታዎች

1924 ኦሊምፒክን ያዘጋጀው ስታዲየም የ1983 የዓለም ዋንጫ ፍጻሜምን አስተናግዷል። በዘንድሮው ኦሊምፒክ ደግሞ ከተደጋጋሚ እድሳቶች በኋላ የሆኪ ውድድርን ያስተናግዳል።

ከ100 ዓመታት በፊት እንደ ውሃ ዋና ላሉ ውድድሮች በርካታ መወዳደሪያዎች ተገንብተዋል።

ዘንድሮ ለዋናተኞች መለማመጃ ቦታ እንዲሆን የተወሰነበት የፒሲን ዴ ቱሬሌስ የመጀመሪያው 50 ሜትር የኦሊምፒክ ገንዳ ለመሆን ችሎ ነበር።

ለዘንድሮው ውድድር አዲስ ተገነቡት ሁለት መወዳደሪያ ቦታዎች ብቻ ናቸው። የባሕር ዳርቻ ቮሊቦል ደግሞ በጊዜያዊነት በኤፍል ታወር አቅራቢያ ይከናወናል።

የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት

የ1924ቱ ውድድሩ ከዘመናዊው ኦሊምፒክ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት የተካሄደበት የመጀመሪያው ኦሊምፒክ ነበር።

ሜዳሊያዎችን ለስፖርተኞች ተሰጥተወዋል። አራት ሰንደቅ ዓላማዎችም እንዲውለበለቡ ተደርጓል። እነዚህም የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የፈረንሳይ (አስተናጋጅ)፣ የግሪክ (የኦሊምፒክ መሥራች እና የመጀመሪያው ውድድር አዘጋጅ) እና የቀጣዩ ውድድር አስተናጋጅ ሆነችው የኔዘርላንድስ ሰንደቅ ዓላማዎች ናቸው።

አየርላድ

አየርላንድ ለ1924ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ ራሷን ችላ ተፎካካሪ እንድትሆን ዕውቅና ተሰጥቷታል። በዚህም በኦሊምፒክ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ በቃች።

የክረምት ኦሎምፒክ

በአውሮፓውያኑ ክረምት 1924 ከፓሪስ ኦሊምፒክ ጋር በመተባበር በቻሞኒክስ የተካሄዱ የስፖርት ውድድሮች በኋላ እንደ መጀመሪያው የክረምት ኦሊምፒክ ተቆጠሩ። በውድድሩ ከ16 አገራት የተውጣጡ ስፖርተኞች በ16 ዘርፎች ተሳትፈዋል።

የኦሊምፒክ የኪነ ጥበብ ውድድሮች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የኦሊምፒክ የኪነ ጥበብ ውድድሮች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በሥነ ሕንፃ፣ በቅርጻ ቅርጽ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በሥዕል እና በሙዚቃ ተወዳድረው ሜዳሊያዎችን ማግኘት የኦሊምፒክ መርሃ ግብር አካል የሆኑ የጥበብ ውድድሮች ነበሩ።

የ1924ቱ ኦሊምፒክ ኦስካር ላሸነፈው ቻሪዮትስ ኦፍ ፋየር (የእሳት ሠረገላዎች) ፊልም መነሻ ሆነ። በ1981 የተሠራው ፊልም ሃሮልድ አብርሃምስ እና ኤሪክ ሊድል የኦሊምፒክ ወርቅ ለማግኘት ያደረጉትን ጥረት ያሳያል።

አብርሃምስ በ100 ሜትር ወርቅ አሸነፈ።

አብርሃምስ በ4x100 ሜትር ዱላ ቅብብልም ታላቋ ብሪታንያ ብር እንድታገኝ ረድቷል።

የኦሊምፒክ የኪነ ጥበብ ውድድሮች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የቡድን ጓደኛው ሊድል በሃይማኖታዊ ምክንት እራሱን ከ100 ሜትር ውድድር አራቀ። ውድድሩ እሑድ በመካሄዱ እና እሑድ ለክርስቲያኖች የእረፍት እና የአምልኮ ቀን በመሆኑ ነው ከውድድሩ ራሱን ያገለለው።

በ200 ሜትር ሊድል ነሐስ ሲያገኝ አብርሃም ስድስተኛ ሆኖ አጠናቀቀ።

ለሊድል በ400 ሜትርም ዕድል ነበረው።

በ400 ሜትር ፍጻሜ ውድድርም ዕድሉን ተጠቀመበት።

ጠንካራ ፉክክር በተደረገበት ውድድር 47.6 ሰከንድ በመግባት የዓለም ክብረ ወሰንን ለማስመዝገብ ቻለ።

የእሳት ሰረገላዎች ፊልም በምርጥ ምሥል እና በምርጥ ሙዚቃን ጨምሮ በአራት ዘርፎች ኦስካርን አሸነፈ።

የኦሊምፒክ የኪነ ጥበብ ውድድሮች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በራሪዎቹ ፊንላንዳውያን

አብርሃም እና ሊድል ብቻ አልነበሩም በአጭር ርቀት ፓሪስ ላይ ጎልተው የወጡት።

ሁለት ፊንላንዳዊያን አትሌቶችም ውድድሩን ይበልጥ ከማድመቅ ባለፈ በመካከለኛ እና በረዥም ርቀት ክብረ ወሰኖችን ሰባብረዋል።

ፓቮ ኑርሚ በአንድ ሺህ 500 ሜትር (3፡53.6) ክብረ ወሰን ሲሰብር፤ ሁለት ሰዓት ሳይሞላው ደግሞ በአምስት ሺህ ሜትርም (14፡31.2) የኦሊምፒክ ክብረ ወሰን አስመዘገበ።

የኦሊምፒክ የኪነ ጥበብ ውድድሮች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

አስገራሚው ኑርሚ በግል አገር አቋራጭ፣ በቡድን አገር አቋራጭ እና በሦስት ሺህ ሜትሮችም ተጨማሪ ሦስት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሳካ።

በአገር አቋራጭ ውድድሩ ወቅት ከፍተኛ ሙቀት በመኖሩ ከ38ቱ ተወዳዳሪዎች 15ቱ ብቻ ለማጠናቀቅ ችለዋል። ውድድሩን ካጠናቀቁት ውስጥ ስምንቱ በቀጥታ በቃሬዛ ተነስተዋል።

ኑርሚን በቅርበት ሲፎካከረው የነበረው በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ አሸንፎ የዓለም ክብረ ወሰን ከ12 ሰከንድ በላይ የሰበረው የአገሩ ልጅ ቪሌ ሪቶላ ነው።

ሪቶላ በሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል፣ በሦስት ሺህ የቡድን ውድድር እና በቡድን አገር አቋራጭ የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል። በአገር አቋራጭ እና በአምስት ሺህ ሜትር ደግሞ ብር ለማግኘት ችሏል።

ኑርሚ እና ሪቶላ በ1920ዎቹ የነበራቸው የበላይነት በራሪዎቹ ፊንላንዳውያን የሚል ቅጽል ስም አስገኝቶላቸዋል።

ሴት አትሌቶች

በ1924 በፓሪስ ከተወዳደሩት 3 ሺህ 89 ስፖርተኞች መካከል 135ቱ ሴቶች ናቸው። ዘንድሮ በውድድሩ ከሚሳተፉት 10 ሺህ 500 ስፖርተኞች ግማሹ ሴቶች ናቸው።

የኦሊምፒክ የኪነ ጥበብ ውድድሮች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ይህን ያውቁ ኖሯል?

  • ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጀርመን በ1920ው እና 1924ቱ ውድድሮች ስፖርተኞቿን እንዳትልክ ታገዳ ነበር። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ደግሞ አገሪቱ ከ1948ቱ ኦሊምፒክ ታግዳለች።
  • በሥነ ሕንፃ፣ በቅርጻ ቅርጽ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በሥዕል እና በሙዚቃ ውድድሮች ሜዳሊያዎች የሚሰጡበት የፓሪስ ኦሊምፒክ የኪነ ጥበብ ውድድሮች ነበሩ። ከ1948 ወዲህ የኪነ ጥበብ ውድድሮች ከኦሊምፒክ ውጪ ሆነዋል።
  • ቴኒስ ከ1924 በኋላ ከኦሊምፒክ መርሃ ግብር ተወግዷል። ምክንያቱ ደግሞ በዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በተቋቋመው አመራር መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ነበር። ወደ ውድድሩ የተመለሰው ከደቡብ ኮሪያው የሴዑሉ የ1988 ኦሊምፒክ በኋላ ነው።
  • በ1920 በኔዘርላንድስ አንትወርፕ ከነበረው 29 የተሳታፊ አገራት ቁጥር በፓሪሱ የ1924 ውድድር ወደ 44 ከፍ ብሏል።
  • በ1924 ውድድር ለአስተናጋጁ አገር ጎልቶ የወጣው አትሌት ሮጀር ዱክሬት አምስት ሜዳሊያዎችን አሸንፎ ነበር። ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ወርቅ ናቸው። ዱክሬት የኦሊምፒክ ሕይወቱን በስምንት ሜዳሊያዎች አጠናቋል። በኦሊምፒክ ታሪክ የትኛውም የፈረንሳይ ስፖርተኛ ከዚህ የሚበልጥ ሜዳሊያ ማሳካት አልቻለም።