ትራምፕ የሰው ሠራሽ አስተውሎትን ጉዳዮች የሚከታተል አዲስ ቡድን አቋቋሙ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ላይ አተኩሮ የሚሠራ እና በብሔራዊ ደኅንነት ዳይሬክተሩ ጄይ ክሌይተን የሚመራ ግብረ ኃይል ማቋቋማቸውን ገለጹ።
"የኤአይ ልዕለ ኃያል" የተባለው ቡድን አሜሪካ ቴክኖሎጂውን በማበልጸግ ረገድ ቀዳሚ መሆኗን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ መንግሥት ከሕዝቡ ጋር ያለውን ግንኙነት በበላይነት እንደሚመራ ትራምፕ እሁድ ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ባገሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ትራምፕ የግብረ ኃይሉ መቋቋምን ያስታወቁት መስከረም 19/2019 ዓ.ም. ኤአይን፣ 'ልዕለ ኃያል' ብለው መሰየማቸውን ካስታወቁ በኋላ ነው።
ከዚህ ቀደም ሰው ሠራሽ የሚለው ቃል "ሐሰተኛ" ይመስላል ሲሉ ተችተው ነበር።
ትራምፕ ባለፈው ሳምንት የግዙፍ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች "አሳሪ ስምምነት" ከተፈራረሙ በኋላ የኤአይን ደኅንነት የሚከታተል ቦርድ እንደሚያቋቁሙ ተናግረው ነበር።
"የኤአይ ልዕለ ኃያል ቡድን የፌደራል መንግሥቱ ከደንበኞች፣ ፍላጎት ካላቸው ቡድኖች፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ወሳኝ መሠረተ ልማት አቅራቢዎች እና ከኃያላን ኩባንያው ጋር ያለውን ግንኙነት ያስተባብራል" ሲሉ ጽፈዋል።
የፌዴራል ንግድ ኮሚሽን ሊቀመንበር አንድሪው ፈርጉሰን፣ የመከላከያ ሚኒስቴር የምርምር እና ምህንድስና ጉዳዮች ምክትል ፀሐፊ ኤሚል ማይክል እንዲሁም የፐርሶኔል አስተዳደር ቢሮ ዳይሬክተር ስኮት ኩፐርም የዚህ ግብረ ኃይል አካል ይሆናሉ።
ይህ ግብረ ኃይል በቀጥታ ለፕሬዝዳንቱ እና ለዋይት ሐውስ የሠራተኞች አስተዳደር ኃላፊ ሱዚ ዋይልስ ሪፖርት ያቀርባል።
የትራምፕ የመጀመሪያ ምርጫ የነበሩት ቢል ፑልቴ በሕግ አውጪዎች ውድቅ ከተደረጉ በኋላ፣ የግብረ ኃይሉ ኃላፊ የሆኑት ክሌይተን በነሐሴ ወር የአሜሪካ ብሔራዊ የመረጃ ዳይሬክተር ሆነው ሥራ ጀምረዋል።
ክሌይተን ቀደም ሲል ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ሲናገሩ "አንድ ነገር በአንድ ጊዜም ዕድልም ሆነ ስጋት በሚሆንበት ጊዜ፣ ጉዳዩን በሚገባ ተረድቶ መቆጣጠር ያስፈልጋል" ብለው ነበር።
ክሌይተን ከዚህ ቀደም በኒው ዮርክ ደቡባዊ ክፍል የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ በቀድሞው የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ላይ የቀረበውን የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ክስ ጨምሮ በርካታ ታላላቅ የሕግ ጉዳዮችን በበላይነት መርተዋል።
የዚህ ግብረ ኃይል መቋቋም ይፋ የተደረገው፣ የኦፕንኤአይ እና አንትሮፒክ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በዘርፉ ውስጥ ባሉ ታዋቂ ሰዎች ዘንድ የቴክኖሎጂውን ቁጥጥር ለማጥበቅ እየጨመረ የመጣውን ግፊት ተከትሎ ነው።
እሁድ ዕለት በወጣ ዘገባ ላይ የኦፕንኤአይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን እንደተናገሩት፣ ኤአይ የሚያስገኘው ጥቅም አንዳንድ አደጋዎቹን ለመቀበል የሚያስችል ምክንያት የሚሰጥ ሲሆን፣ ቴክኖሎጂው ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ሊቀጥል እንደሚገባም ተከራክረዋል።
"ሰዎች በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የበለጠ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ለማስቻል፣ በዚህ ቴክኖሎጂ ምክንያት አንዳንድ አሉታዊ ነገሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉ መቀበል አለብን" ሲሉ አልትማን ለፖሊቲኮ የቴክኖሎጂ ጋዜጣ 'ዲኮድድ' ተናግረዋል።
ትራምፕ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግበት የሚቀርቡትን ጥሪዎች ውድቅ አድርገው በአብዛኛውን ራሳቸው እንዲቆጣጠሩ ለአይቲ ኩባንያዎች ኃላፊነቱን ሰጥተዋል።


































