የስፔን ፖሊስ የያዛቸው በባሕር ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ ድሮኖች

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, በስፔን ፖሊስ የተያዙት በውሃ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ ድሮኖች
የስፔን ፖሊስ የያዛቸው በባሕር ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ ድሮኖች

የስፔን ፖሊስ በውሃ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅን ለማዘዋወር ይጠቅማሉ ተብለው የተሰሩ ሰው አልባ ጀልባዎችን (ድሮኖች) መያዙን አስታውቋል።

ስም ያልተሰጣቸው እነዚህ ድሮኖች እስከ 200 ኪሎ ግራም ክብደት የመሸከም አቅም አላቸው። ይህንኑ በተመለከተ ፖሊስ 14 ወራትን ምርመራ ካደረገ በኋላ በተለያዩ የስፔን ከተሞች ውስጥ ስምንት ሰዎችን አስሯል።

የስፔን ፖሊስ ያለ ሰው እርዳታ መንቀሳቀስ የሚችሉና በባሕር ውስጥ መጓዝ ሚችሉ ድሮኖችን ሲያገኝ ይህ የመጀመሪያው መሆኑን ገልጿል።