የዓለማችንን ስጋት ለመቅረፍ ከሥጋ ይልቅ ነፍሳትን መመገብ ይኖርብን ይሆን?

የዓለማችንን ስጋት ለመቅረፍ ከሥጋ ይልቅ ነፍሳትን መመገብ ይኖርብን ይሆን?

በሁሉም ባይሆንም በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች ውስጥ ነፍሳት ለምግብነት ይውላሉ። በተወሰኑ የአፍሪካ እና የእስያ አገራት ውስጥም ለረጅም ዘመን ነፍሳት የሕዝቡ የምግብ አካል ሆነው ቆይተዋል።

አሁን ባለንበት ዘመን አሳሳቢ እየሆነ ለመጣው የአየር ንብረት ለውጥ የምድር ነዋሪ የሥጋ ፍጆታ የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው ይነገራል። ከዚህም የተነሳ ነፍሳትን ለምግብነት ማዋል ካሉት በርካታ ጠቀሜታዎች ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አንድ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

ከዚህ አኳያ ነፍሳት ወደፊት የምግባችን አንድ አካል መሆን ይኖርባቸው ይሆን?