በቱርክ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ ያደረሰው ጉዳት ከሰማይ ሲታይ

በቱርክ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ ያደረሰው ጉዳት ከሰማይ ሲታይ

በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አካባቢ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት ፍለጋ እየተካሄደ ነው።

አዲስ የወጡ የድሮን ቀረጻዎች እንደሚያሳዩት በሺዎች የሚቆጠሩ ሕንጻዎች ወድመዋል።

አንዳንድ መንደሮች ደግሞ እንዳልነበሩ ሆነው ወደ ሜዳነት ተቀይረዋል።

አካባቢው ከፍተኛ ቅዝቃዜ የያዘበት ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሰዎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ። የሟቾች ቁጥርም ከ9 ሺህ አልፏል።