ከ40 ሺህ በላይ ሶማሊያውያንን የገደለው ድርቅ በአፍሪካ ቀንድ የደቀነው ስጋት
ከ40 ሺህ በላይ ሶማሊያውያንን የገደለው ድርቅ በአፍሪካ ቀንድ የደቀነው ስጋት
ለተከታታይ ዓመታት በሶማሊያ ዝናብ አለመጣሉን ተከትሎ በድርቅ ምክንያት ከ43 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
ከሟቾቹ መካከል ግማሽ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ናቸው። ለረሃብ ለተጋለጡ ሶማሊያውያን አስፈላጊውን እርዳታ በቶሎ ማቅረብ ካልተቻለ በቀጣይ ወራት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ ተሰግቷል።



