ባለቤታቸውን እና 13 ልጆቻቸውን በጎርፍ አደጋ አጥተው ብቻቸውን የቀሩት አባወራ
ባለቤታቸውን እና 13 ልጆቻቸውን በጎርፍ አደጋ አጥተው ብቻቸውን የቀሩት አባወራ
ባለፈው ሳምንት ኮንጎ ውስጥ በደረሰ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ400 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። የጠፉትን ሰዎች ለማግኘት ጥረቱ እንደቀጠለ ነው።
በአደጋው አንድ አባት ብቻ 13 ልጆቹን አጥቷል። ቤተሰቦችም በርካታ የቤተሰብ አባሎቻቸውን አጥተው እና ቤት ንብረታቸው ወድሞ ከባድ ሐዘን ውስጥ ናቸው።



