የምግብ ዋጋ መናርን ለመቋቋም አማራጮችን እየተገበሩ ያሉ የሦስት አገር ነዋሪዎች
የምግብ ዋጋ መናርን ለመቋቋም አማራጮችን እየተገበሩ ያሉ የሦስት አገር ነዋሪዎች
በዓለም ዙሪያ ተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በተከሰተ ምጣኔ ሀብታዊ መቀዛቀዝ ምክንያት የምርቶች አቅርቦት ክፉኛ ተስተጓጉሎ ቆይቶ ነበር።
ዓለም ኮቪድ ካስከተለው ተጽእኖ ሳታገግም የተከሰተው የዩክሬን እና የሩሲያ ጦርነት ደግሞ የምግብ እና የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል።
በዚህም ሳቢያ በመላው ዓለም የምግብ ምርቶች እጥረት እና የዋጋ ንረትም ተከስቷል። ይህንንም ተከትሎ ቢሊዮኖች ከኑሮ ውድነት ጋር እየታገሉ ነው። ይህ ቪዲዮ የተከሰተውን ቀውስና አንዳንዶች ለጊዜው መፍትሔ ብለው እየተገበሩት ያለውን አማራጭ የስቃኛል።



