ከአውዳሚ ጦርነት ማግስት ወደ ሌላ የውዝግብ አዙሪት ውስጥ የገባችው ጋዛ
ከአውዳሚ ጦርነት ማግስት ወደ ሌላ የውዝግብ አዙሪት ውስጥ የገባችው ጋዛ
ጋዛ ለ15 ወራት በጦርነት ውስጥ አልፋለች። 85 በመቶ የሚሆኑ ነዋሪዎቿ ተፈናቅለዋል። ከ45 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የግዛቷ ሁለት ሦስተኛ የሚሆነው ግንባታ ወድሟል። ይህንን መልሶ ለመገንባት ዓመታትን ይፈልጋል። በዚህ ሁኔታ ላይ የምትገኘው ጋዛ አሁን ደግሞ ሌላ የውዝግብ አጀንዳ ተከፍቶላታል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "እቆጣጠራታለሁ" ብለዋል።



