ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱት ህጻናት ከ7 ቀዶ ሕክምና በኋላ ተለያዩ

ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱት ህጻናት ከ7 ቀዶ ሕክምና በኋላ ተለያዩ

ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱት ብራዚላዊ መንታ ሕጻናት በበይነ መረብ በታገዘ ቀዶ ሕክምና በተሳካ ሁኔታ ተለያዩ።

ሦስት ዓመት የሆናቸው በርናርዶ እና አርቱር ለንደን ውስጥ በሚገኘው ግሬት ኦርሞንድ ስትሪት ሆስፒታል መሪነት ሪዮ ዲ ጄኔሪዮ ውስጥ በበይነ መረብ በታገዘ ቀዶ ሕክምና መለያየት ችለዋል።

ሕጻናቱ የመጨረሻውን ቀዶ ሕክምና ጨምሮ ሰባት ቀዶ ሕክምናዎችን አድርገዋል። ሕጻናቱ በማገገም ላይ ሲሆኑ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራትም ክትትል ይደረግላቸዋል ተብሏል።