የቀጠለው የኬንያውያን ወጣቶች ተቃውሞ
የቀጠለው የኬንያውያን ወጣቶች ተቃውሞ
የኬንያ መንግሥት በተለያዩ ምርት እና አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ለመጣል ያዘጋጀው ረቂቅ ሕግ በአገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞን ቀስቅሷል።
በተለይ በረቂቅ ሕጉ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲወያዩ የነበሩት ኬንያውያን ወጣቶች ከየትኛውም የፖለቲካ ቡድን ነጻ የሆነ ተቃውሞን እየመሩ ነው።
የዊሊያም ሩቶ መንግሥት ባለፈው ሳምንት የተቀሰቀሰውን ታውሞ ተከትሎ ከታቀዱት ታክሶች መካከል የተወሰኑትን እንዲቀሩ ቢያደርግም ተቃውሞው ግን ቀጥሏል።
የወጣቶቹ ጥያቄ አዲሱ የታክስ ረቂቅ ሙሉ በሙሉ ውድቅ መሆን አለበት ከማለታቸው ባሻገር በመንግሥት ውስጥ ያለውን ሙስና እና ብክነት የሚያስቀሩ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እየጠየቁ ነው።
ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም. ለአገሪቱ ፓርላማ ቀርቦ ውይይት ይደረግባትል የተባለው ረቂቅ የፋይናንስ ሕግ ለመቀወም ወጣቶቹ በጠሩት ሰልፍ ምክንያት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል።
ወጣቶቹ ፓርላማውን ለመውረር ዕቅድ ያላቸው ቢሆንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል ፓርላማው በሚገኝበት የከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ ተሰማርቷል።



