በቀውስ ውስጥ የምትገኘው የዲሞክራቲክ ኮንጎዋ ቁልፍ ከተማ ጎማ ከከባድ ጦርነት በኋላ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
በቀውስ ውስጥ የምትገኘው የዲሞክራቲክ ኮንጎዋ ቁልፍ ከተማ ጎማ ከከባድ ጦርነት በኋላ

ኤም23 የሚባሉት የዲሞክራቲክ ኮንጎ አማጺያን ከሳምንት በፊት ጎማ የተባለችውን የድንበር ከተማ ተቆጣጥረዋል። ከተማዋ በአካባቢው ትልቋ እና ስትራቴጅክ ናት።

አማጽያኑ ጎማን ለመቆጣጠር በከፈቱት ጦርነት ምክንያት 400 ሺህ ሰዎች ከከተማ በመውጣት ተሰደዋል። የቢቢሲ ዘጋቢ አሁን በኤም23 ቁጥጥር ስር ባለችው ጎማ ከተማ ተገኝቶ በጦርነቱ የተከሰተውን ጉዳት ተመልክቷል።