ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሐማስ ከዚህ በፊት ታይታ በማይታወቅ ሁኔታ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃትን ከፍቶ ውጥረት በማይለየው የመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ጦርነት ተቀስቅሷል።
ሐማስ ጥቃቱን በከፈተበት በአጭር ጊዜ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ከጋዛ ከተማ በመተኮስ በርካታ የእስራኤል ከተሞችን የመታ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹም ወደ እስራኤል ግዛት ዘልቀው መግባታቸው ተዘግቧል።
እስራኤልም በአጸፋው በጋዛ ላይ የአየር ጥቃት የከፈተች ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁም አገራቸው “ጦርነት ውስጥ” መሆኗን ተናግረዋል። ይህ ግጭት እንዴት ጀመረ?









