በዓለም ረዥሙ በመስታወት የተሰራው ድልድይ
በዓለም ረዥሙ በመስታወት የተሰራው ድልድይ
ቬትናም ውስጥ በሁለት ትልልቅ ኮረብታዎች መካከል የተሰራው የመስታወት ድልድይ በዓለም የክብረ ወሰን መዝገብ ላይ ሰፍሯል።
ጊነስ ወርልድ ሪኮርድስ የመዘገበው ይህ ድልድይ 632 ሜትር ይረዝማል። በጥልቅ ሸለቆ ላይ የተገነባው የመስታውት ድልድዩ 150 ሜትር ከፍታ አለው።
ከርዝመቱ እና ቁመቱ በተጨማሪ የአካባቢውን ሥነ ምህዳር ጠብቆ የተሰራ በመሆኑ እጅግ ማራኪ የቱሪስት መዳረሻ ነውም ተብሏል።



