ናሳ ለምን የዓለማችንን የውሃ ይዞታ ከጠፈር ላይ ሆኖ ሊመዘገብ ፈለገ?

ናሳ ለምን የዓለማችንን የውሃ ይዞታ ከጠፈር ላይ ሆኖ ሊመዘገብ ፈለገ?

በናሳ የሚመራው የሳተላይት ተልዕኮ በመላው ዓለም የሚገኙ ወንዞች፣ ሐይቆች እና የውሃ ማጠራቀሚያዎች የያዙትን የውሃ መጠን ለማወቅ የሚያስችል ጥናት ማካሄድ ጀምሯል።

አዲሱ ሳተላይት ዘመናዊ ራዳር የተገጠመለት ሲሆን ሳይንቲስቶች የዓለምን የውሃ መጠን በመለየት እና በዚህ መነሻነት ለአየር ንብረት ለውጥ ተጨማሪ መንስኤዎችን እንዲሁም መፍትሄዎችን ለመለየት ያስችላቸዋል ተብሏል።