እርጅናን ለማሸነፍ በየዓመቱ ሚሊዮን ዶላሮችን የሚያፈሰው ባለሃብት
እርጅናን ለማሸነፍ በየዓመቱ ሚሊዮን ዶላሮችን የሚያፈሰው ባለሃብት
ሚሊየነሩ ብሪያን ጆንሰን እርጅናውን ለመቀልበስ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በማውጣት ጥረት እያደረገ ነው።
ብሪያን አሁን ዕድሜው 45 ነው። በስፖርት እና በሕክምና ግን ወደ 18 ዓመት መመለስ ይፈልጋል። ይህንንም ለማሳካት ሂደቱን የሚከታተሉ 30 አባላት ያሉት የሐኪሞች እና ሳይንቲስቶች ቡድን ቀጥሯል።



