የ16ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ።
አራት ጨዋታዎች ቅዳሜ ሲከናወኑ፤ አምስት ጨዋታዎች እሑድ እንዲሁም ቀሪው አንድ ጨዋታ ሰኞ ይከናወናሉ።
የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የእነዚህን ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።
ቅዳሜ
ቼልሲ ከ ኤቨርተን
ቼልሲ ከአርሰናል ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ድንቅ የነበረ ቢሆንም ከዚያ ወዲህ ግን ውጤታማ መሆን አልቻለም።
ኤንዞ ማሬስካ ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።
ኤቨርተን በተለይም ኬይራን ደውሰበሪ-ሃል እና ኢሊማን ንዳዬ በጥሩ አቋም ላይ ይገኛሉ።
ከሰሞኑ ቼልሲ አሳማኝ ባይሆንም ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 -1
ሊቨርፑል ከ ብራይተን
ሞ ሳላህ ውዝግብ በፈጠረበት ሊቨርፑል አሠልጣኙ አርን ስሎት ይህንን ጨምሮ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።
ብራይተን ግን የሚገመት ቡድን አይደለም።
ሊቨርፑል ወጥ ሆነ አቋም እያሳየ መቀጠል ይኖርበታል።
ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል።
ግምት፡ 2- 2
በርንሌይ ከ ፉልሃም
በርንሌይ ከወራጅ ቀጠና ቡድኖች ጋር ለመፎካከር ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።
ፉልሃምም ወደ ወረጃ ቀጠና የመግባት ስጋት ስላለበት ወሳኝ ጨዋታ ይሆናል።
ፉልሃም ከማንቸስተር ሲቲ እና ከፓላስ ጋር ካሳየው ተፎካካሪነት አንጻር ከዚህ ጨዋታ ነጥብ የሚያገኝ ይመስለኛል።
ግምት፡ 1 - 1

አርሴናል ከ ዎልቭስ
በደረጃ ሰንጠረዡ አናት እና ግርጌ ላይ በሚገኙ ቡድኖች መካከል የሚደረግ ጨዋታ ነው።
ዎልቭሶች መጥፎ የውድድር ዓመት እያሳለፉ ነው።
አርሴናል ብዙ ተጫዋቾችን በጉዳት ቢያጣም በሻምፒዮንስ ሊግ ክለብ ብሩዥን ማሸነፍ ችሏል።
መድፈኞቹ በቀላሉ የሚያሽንፉበት መርሐ ግብር ነው።
ግምት፡ 3- 0
እሑድ
ክሪስታል ፓላስ ከ ማንቸስተር ሲቲ
ፓላስ ብዙ ጨዋታዎችን እንደሚያሽንፍ ብገምትም የዩሮፓ ኮንፈረንስ ጨዋታዎች ጉዟቸውን እያስተጓጎሉት ነው።
ሲቲም በሻምፒዮንስ ሊግ በመሳተፉ ድካሙ ለሁለቱም ቡድኖች ነው።
ኧርሊንግ ሃላንድ ጎል እንደሚያስቆጥር ብጠብቅም የሲቲ ከሜዳ ውጭ አቋም አሳማኝ አይደለም።
ፓላስ በኤፍኤ ካፕ ሲቲን ማሸነፉ መነቃቃትን የሚፈጥርላቸው ይሆናል።
ግምት፡ 1- 1
ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ቶተንሃም
ፎረስት በአውሮፓ መድረክ መሳተፉ የሊግ ጉዞው ላይ ጫና ይኖረዋል።
ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ቢያሽንፍም ቶተንሃም ምንም ተገማች ቡድን አይደለም።
ይህም በአቻ ውጤት ሊጠናቀቅ የሚችል ጨዋታ እንደሆነ ይሰማኛል።
ግምት፡ 1 - 1

ሰንደርላንድ ከ ኒውካስል
ኒውካስል በሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ መድረክ ከመጫወቱም በላይ ከሜዳው ውጭ ውጤታማ መሆን አልቻለም።
ሰንድርላንድ ሳምንቱን በዝግጅት ማሳለፉ የበለጠ ዕድል እንዲኖረው ያደርጋል።
ይህ ጨዋታ የሳምንቱ ምርጥ ጨዋታ እንደሚሆን እገምታለሁ።
ጨዋታው በጥቋቁር ድመቶቹ የበላይነት ይጠናቀቃል።
ግምት፡ 2 - 1
ዌስት ሃም ከ አስቶን ቪላ
የኡናይ ኤምሬ ቡድን በሊጉ ውጤታማ ጉዞ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ዌስት ሃምም በአዲሱ አሠልጣኝ ኑኖ እስፕሪንቶ ሳንቶ ስር ውጤታማ መሆን ጀምሯል።
ቪላ በርካታ ጎል የሚያስቆጥሩ ተጫዋቾችን ይዟል።
ግምት፡ 1 - 2
ብሬንትፎርድ ከ ሊድስ
ሊድስ ባለፉት ጨዋታዎች ጥሩ ተፎካካሪ መሆኑን አሳይቷል።
ብሬንትፎርድ በሜዳው ያለው አቋም ጥሩ በመሆኑ ለዚህ ጨዋታ ጥሩ ግምት ይሰጠዋል።
በሜዳቸው ሊቨርፑል፣ ኒውካስል እና በርንሌይን ማሸነፍ ችለዋል።
በዚህ ጨዋታ ብሬንትፎርድ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 - 0

እሑድ
ማንቸስተር ዩናይትድ ከ በርንመዝ
በርንመዝ ውጤታማ ጉዞ እያደረገ ባይሆንም ባለፉት የኦልድ ትራፎርድ ጨዋታዎች የበላይነት ነበረው።
በዚህ ጨዋታም ለተከታታይ ሦስተኛ ጊዜ እንደሚያሽንፉ እገምታለሁ።
የሩበን አሞሪም ቡድን መሻሻሎችን እያሳየ ይገኛል።
ቡድኑ አሁንም አሳማኝ መሆን ባይችልም በጥሩ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ግምት፡ 1 - 2















