ጋዛ ውስጥ የተገደለው የሐማስ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነበር?
ጋዛ ውስጥ የተገደለው የሐማስ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነበር?
ከሃያ ዓመታት በላይ በእስራኤል እስር ቤት ቆይቶ ከተፈታ በኋላ በሐማስ ውስጥ የቡድኑ የውስጥ ደኅንነት ኃላፊ፣ የወታደራዊ ኃይል አዛዥ እንዲሁም ከኢስማኤል ሃኒያ ግድያ በኋላ ደግሞ የሐማስ አጠቃላይ መሪ የሆነው ያህያ ሲንዋር በእስራኤል ጦር መገደሉ ተገልጿል።
ለዓመታት በእስራኤል በብርቱ ከሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚ የነበረው ሲንዋር፣ ባለፈው ዓመት መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ሐማስ የፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃት ከኋላ ሆኖ መርቶታል በሚል ባለሥልጣናት ሲፈልጉት ቆይተዋል።



