ሦስት ሳምንታትን ያስቆጠረው የሱዳን ግጭት ያስከተለው ቀውስ
ሦስት ሳምንታትን ያስቆጠረው የሱዳን ግጭት ያስከተለው ቀውስ
በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሦስት ሳምንታትን አስቆጥሯል። ሦስት ጊዜ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጎ ነገር ግን በተደጋጋሚ ተጥሷል።
ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች አገራቸውን ለቀው ሲሰደዱ ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። በ10 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሱዳናውያን የአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ጠባቂ ሆነዋል።
አሁንም ለሰባት ቀናት የሚቆይ ተኩስ አቁም ተደርጓል ቢባልም በካርቱም እና በሌሎች ከተሞች ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው። ሁለቱም ኃይሎች ግጭቱን በቅርብ ጊዜ ያቆማሉ ተብሎ አይጠበቅም።



