ብዙ ያልተነገረለት 'የአፍሪካው ታይታኒክ' አደጋ ለምን ተድበስብሶ ቀረ?
ብዙ ያልተነገረለት 'የአፍሪካው ታይታኒክ' አደጋ ለምን ተድበስብሶ ቀረ?
ሁለት ሺህ ይደርሳሉ የተባሉ ሰዎችን አሳፍሮ ከሴኔጋል መዲና ዳካር ተነስቶ ሲጓዝ በነበረው ግዙፍ ጀልባ ላይ የደረሰው አሰቃቂ የጀልባ አደጋ እነሆ 20 ዓመት ሆነው።
ይህ በባሕር ላይ በደረሱ አደጋዎች ታሪክ ሁለተኛው አሰቃቂ ክስተት ነው። በርካቶች አስካሁን ያልረሱት ሐዘን ውስጥ ይገኛሉ።
የአሁኑ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አልዩ ሲሴ በአደጋው 11 ቤተሰቦቹን አጥቷል።
1863 ሰዎች በዚህ አደጋ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በተዓምር ከእዚህ አደጋ መትረፍ የቻሉት 64 ሰዎች ብቻ ናቸው።
ለአደጋው ካፒቴኑ ተጠያቂ ነው ቢባልም በብዙ ምክንያት ጉዳዩ ሲድበሰበስ ቆይቷል። ከ20 ዓመታት በኋላ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ምን ይላሉ?



