ለኮቪድ መከላከያ ያገለገሉ ማስኮችን በመጠቀም የቤት ውስጥ መገልገያ እንዴት ይሠራል?
ለኮቪድ መከላከያ ያገለገሉ ማስኮችን በመጠቀም የቤት ውስጥ መገልገያ እንዴት ይሠራል?
በኮሮኖቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በዓለም ዙሪያ በየወሩ 129 ቢሊዮን ማስኮች ከአገልግሎት ላይ ከዋሉ በኋላ ይጣል ነበር። አሁንም ይህ ማስኮችን የመጠቀም ሁኔታ እንደቀጠለ ነው።
ነገር ግን እነዚህ ጥቅም ላይ የዋሉ ማስኮች በየቦታው እየተጣሉ ይገኛሉ። ብዙው ደግሞ ወደ ውቅያኖሶች እና ወደ ተለያዩ የውሃ አካላት ውስጥ በመግባት ብክለትን እያስከተሉ ነው።
የ23 ዓመቱ ደቡብ ኮሪያዊው ወጣት ለዚህ መፍትሄ አምጥቷል። ኪም ሃ-ኑኤል ማስክን በመሰብሰብ የቤት ውስጥ እቃዎችን እያመረተበት ነው። እንዴት?



