ዶናልድ ትራምፕን ለእስር ሊዳርጋቸው ይችላል የተባለው ግንኙነት እንዴት ተጋለጠ?
ዶናልድ ትራምፕን ለእስር ሊዳርጋቸው ይችላል የተባለው ግንኙነት እንዴት ተጋለጠ?
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስቶርሚ ዳንኤልስ ከተባለች ተዋናይት ጋር ነበራቸው የተባለውን ግንኙነት በተመለከተ መረጃ እንዲደበቅ አድርገዋል በሚል ምርመራ ሲካሄድባቸው ቆይቷል።
ዶናልድ ትራምፕ ዳንኤልስ ምስጢር እንዳተወጣ በሚል ከ2016ቱ ምርጫ በፊት 130 ሺህ ዶላር ሰጥተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
ክፍያውን የፈጸመው የቀድሞ ጠበቃቸው ማይክል ኮኸን በዚሁ ጉዳይ እና ሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ታስሮ ነበር።
ዶናልድ ትራምፕ ግን ውንጀላው መሰማት ከጀመረበት 2018 ጀምሮ ድርጊቱን እንዳልፈጸሙ እያስተባበሉ ቆይተው ጉዳዩ አሁን ከጫፍ ደርሷል።
ሊታሰሩ ይችላሉ የሚል ጭምጭምታዎችም እየተሰሙ ነው።



