የአፍሪካ ቀንድ መሪዎች በተመሳሳይ ቀን ያደረጓቸው ጉብኝቶች ሲቃኙ
የአፍሪካ ቀንድ መሪዎች በተመሳሳይ ቀን ያደረጓቸው ጉብኝቶች ሲቃኙ
የአፍሪካ ቀንድ መሪዎች በአንድ ቀን የተለያዩ ጉብኝቶችን አድርዋል። ሰኞ መጋቢት 04/2015 ዓ.ም. ዋነኞቹ የአፍሪካ ቀንድ አገራት መሪዎች በተለያዩ ከተሞች ተገናኝተው መክረዋል።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ደቡብ ሱዳን አምርተው ከፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ከምክትላቸው ሬክ ማቻር ጋር ተወያይተዋል።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደግሞ በተመሳሳይ ዕለት የሱዳን ሽግግር ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት ሌ/ጄኔራል ሃምዳን ዳጋሎን እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድን በአሥመራ ተቀብለው አነጋግረዋል።



