የኢድ አልፈጥር አከባበር በዓለም ዙሪያ በምስል

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ የሆነው የረመዳን ወር መጠናቀቁን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ የኢድ አልፈጥር በዓል ተከብሯል።

1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በጦርነት በወደመችው ጋዛን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በጸሎት፣ ከቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ ጋር ማዕድ በመቋደስ እና በሌሎች ክብረ በዓላት ተከብሯል።

የተወሰኑትን በፎቶ እንቃኛቸው።

በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ የነበረው የኢድ አልፈጥር የማለዳ የጸሎት ፕሮግራም

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ የነበረው የኢድ አልፈጥር የማለዳ የጸሎት ፕሮግራም
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ ተብላ በምትጠራው መካ የተሰባሳቡ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ኢድ አልፈጥርን ተሰባስበው አክብረውታል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ ተብላ በምትጠራው መካ የተሰባሳቡ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ኢድ አልፈጥርን ተሰባስበው አክብረውታል
በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ ሙስሊሞች ለስግደት እየተዘጋጁ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ ሙስሊሞች ለስግደት እየተዘጋጁ
በኬንያዋ የባህር ዳርቻ ከተማ ሞምባሳ በመቶዎች ሙስሊሞች እለቷን እንዲህ አስበዋታል

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በኬንያዋ የባህር ዳርቻ ከተማ ሞምባሳ በመቶዎች ሙስሊሞች እለቷን እንዲህ አስበዋታል
በጦርነት ባለችው ሱዳን፣ በምስራቃዊቷ ፖርት ሱዳን በሚገኝ ስታዲየም እየጸለዩ ያሉ ሙስሊሞች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በጦርነት ባለችው ሱዳን፣ በምስራቃዊቷ ፖርት ሱዳን በሚገኝ ስታዲየም እየጸለዩ ያሉ ሙስሊሞች
በኔዘርላንድስ፣ሮተርዳም ከተማ የነበረው የኢድ አልፈጥር አከባበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በኔዘርላንድስ፣ሮተርዳም ከተማ የነበረው የኢድ አልፈጥር አከባበር
ለባለፉት ጥቂት ዓመታት በጦርነት ባለችው ዩክሬን ውስጥ የኢድ አልፈጥር ስጦታ ሲቀባበሉ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ለባለፉት ጥቂት ዓመታት በጦርነት ባለችው ዩክሬን ውስጥ የኢድ አልፈጥር ስጦታ ሲቀባበሉ
በጦርነቱ ወደ ፍርስራሽነት በተቀየረችው የጋዛ ሰርጥ በጃባሊያ በእስራኤል ጥቃት ወደ ፍርስራሽነት በተቀየረ መስጊድ ፍልስጤማውያን ተሰባስበው እለቷን አስበዋታል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በጦርነቱ ወደ ፍርስራሽነት በተቀየረችው የጋዛ ሰርጥ በጃባሊያ በእስራኤል ጥቃት ወደ ፍርስራሽነት በተቀየረ መስጊድ ፍልስጤማውያን ተሰባስበው እለቷን አስበዋታል።
በኢየሩሳሌም አል አቅሳ መስጊድ የነበረው አከባበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በኢየሩሳሌም አል አቅሳ መስጊድ የነበረው አከባበር
በኳታር ስታዲየም የነበረ የጸሎት ስነ ስርዓት

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በኳታር ስታዲየም የነበረ የጸሎት ስነ ስርዓት
በፖርቹጋሏ ሊዝበን ሙስሊሞች በአብሮነት ዕለቷን አስበዋታል

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በፖርቹጋሏ ሊዝበን ሙስሊሞች በአብሮነት ዕለቷን አስበዋታል
በጣልያን፣ ኔፕልስ ፕሌብሲቶ አደባባይ በርካቶች አንድ ላይ ኢድ አልፈጥርን አክብረዋል

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በጣልያን፣ ኔፕልስ ፕሌብሲቶ አደባባይ በርካቶች አንድ ላይ ኢድ አልፈጥርን አክብረዋል
በፓኪስታን፣ ፔሽዋር በሚገኝ መስጊድ ከአፍጋኒስታን የተሰደዱ ተፈናቃዮች ጸሎት ሲያደርሱ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በፓኪስታን፣ ፔሽዋር በሚገኝ መስጊድ ከአፍጋኒስታን የተሰደዱ ተፈናቃዮች ጸሎት ሲያደርሱ