ዓለምን እያነጋገረ ያለው የትራምፕ እና የዜሌንስኪ ጭቅጭቅ በዋሽንግተን
ዓለምን እያነጋገረ ያለው የትራምፕ እና የዜሌንስኪ ጭቅጭቅ በዋሽንግተን
ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመወያየት ወደ ዋሽንግተን ተጉዘው የነበሩት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ከፕሬዝዳንቱ እና ከምክትላቸው ጋር በጋዜጠኞች ፊት የገቡበት ውዝግብ መነጋገሪያ ሆኗል።
ከዚህ በፊት ባልታየ ሁኔታ ዜሌንስኪ፣ ትራምፕ እና ምክትላቸው ጄ ዲ ቫንስ በፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ውስጥ ተወዛግበዋል።
በዚህም ዩክሬን ጦርነቱን እያሸነፈች እንዳልሆነ እና አሜሪካ የጦር መሳሪያ ባትሰጣቸው ኖሮ ጦርነቱ በሁለት ሳምንት ያበቃ እንደነበር ትራምፕ በኃይለ ቃል ሲናገሩ ተሰምተዋል።
ዜሌንስኪም በቁጣ ውስጥ ሆነው አገራቸውን ለመከላከል የቻሉትን እያደረጉ መሆናቸውን እና ትራምፕ እና ምክትላቸው ያሉበትን ሁኔታ እንዳልተረዱት ምላሽ ሲሰጡ ነበር። ቪዲዮውን ይመልከቱ . . .



