ጀርመን ከ ስፔን፡ ከፍጻሜ በፊት ያለውን የፍጻሜ ጨዋታ ማን ያሸንፋል?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ውድድሮች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ መካሄድ ይጀምራሉ።
ከሩብ ፍጻሜው አልፈው ወደ ዋንጫው የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያቃኑት ቡድኖች የትኞቹ ይሆናሉ?
የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ከምድብ ጨዋታዎች ጀምሮ ሲያደርግ እንደነበረው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎችንም እንደሚከተለው ገምቷል።
ስፔን ከ ጀርመን

ስፔን በውድድሩ ምርጥ ቡድን ናት።
ጀርመን በሁሉም የሜዳው ክፍሎች ጠንካራ ተጫዋቾችን ስትይዝ፤ ስፔንም በተመሳሳይ ጥራት ያላቸውን ተጫዋቾች አካታለች።
መሃል ሜዳውን ሮድሪ እና ፋብያን ሩዊዝ ሲያሾሩት ሁለቱን ክንፎች ደግሞ ላሚን ያማል እና ኒኮ ዊሊያምስ ይፈነጩበታል።
ጀርመን በሜዳዋ ብትጫወትም፤ ስፔንን ለማቆም ከባድ ይመስላል።
ግምት፡ 2 – 1
ፖርቹጋል ከ ፈረንሳይ

የፖርቹጋሉ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከአጥቂያቸው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዕድሜ እና አቋሙ አንጻር ቆፍጠን ብለው መወሰን ይኖርባቸዋል።
በውድድሩ ፈረንሳይ እንደተጠበቀችው ባትሆንም ከቤልጂየም ጋር በነበራት ጨዋታ ጠንካራ የተከላካይ መስመር እንዳላት አሳይታለች።
በውድድሩ ላይ ሦስት ጎሎችን ብቻ (ሁለቱ በራስ ላይ የተቆጠሩ ሲሆኑ ቀሪዋ ከፍጹም ቅጣ ምት የተገኘች) ቢያስቆጥሩም አሁን የሚያንሰራሩበት አጋጣሚ ይመስለኛል።
በዚህ ጨዋታም ሮናልዶ ከቆመ ኳስ ዒላማውን የጠበቀ ሙከራ አያደርግም።
ግምት፡ 0 – 2
እንግሊዝ ከ ስዊትዘርላንድ

ስዊትዘርላንድ የተደራጀ ቡድን ከመያዟም በላይ በልበ ሙሉነት ነው የሚጫወቱት።
እንግሊዝ ደግሞ ብዙ ማሻሻል የሚገቧት ቦታዎች አሉ።
ቡድኑ እስካሁን ካየነው ብዙም ተለውጦ የሚቀርብ አይመስለኝም።
እንደ ስፔን የሚያምር ጨዋታ ባያሳዩም ስዊትዘርላንድን የሚያንበረክክ ድንቅ ተጫዋቾችን ቡድኑ ይዟል።
ግምት፡ 1 – 0
ኔዘርላንድስ ከ ቱርክ

ቱርክ በጥሎ ማለፉ ኦስትሪያን አሸንፋ ለሩብ ፍሜው የደረሰችበትን መንገድ አስደናቂ ነው።
ቡድኑ በመከላከል ረገድ የተደራጀ ከመሆኑም በላይ በመልሶ ማጥቃትም አስፈሪ መሆናቸውን አሳይተዋል።
ኔዘርላንድ እስካሁን አሳማኝ እንቅስቃሴ ባታደርግም ጥራት ያላቸው ተጫዋቾችን ይዛለች።
ይህንን ጨዋታ ለመገመት ከባድ ቢሆንም ኔዘርላንድ ሁለት ጎል አስቆጥራ ግማሽ ፍጻሜውን ትቀላቀላለች።
ግምት፡ 2 – 1












