500 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙት እና ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት የሐማስ ዋሻዎች

እስራኤል በጋዛ ላይ ለመፈጸም እየተዘጋጀችበት ላለው የእግረኛ ጦር ወረራ ከመሬት በታች ያሉ ዋሻዎችን ማፈራረስ ዋነኛ ኢላማዋ አድርጋለች።

ነገር ግን የዋሻዎቹ መግቢያዎች ጋዛ ውስጥ በሚገኙ የመኖሪያ ሕንጻዎች ውስጥ በመሆናቸው እና በቅርቡ ሐማስ ያገታቸውን ሰዎች በዋሻዎቹ ውስጥ ደብቋል ተብሎ ስለሚታመን ዘመቻው ውስብስብ ሊሆን ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። ለመሆኑ ዋሻዎቹ ምን ይመስላሉ?