ቢቢሲ ያጋለጠው የአፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ሰቆቃ በባሕረ ሰላጤዋ አገር
ቢቢሲ ያጋለጠው የአፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ሰቆቃ በባሕረ ሰላጤዋ አገር
በባሕረ ሰላጤው አገራት ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ይገኛሉ። ኑሮን ለማቃናት ወደ አረብ አገራቱ ያቀኑት አፍሪካውያን ግን ሥራ እና ኑሮ ቀላል አልሆነላቸውም።
አብዛኞቹ በአሠሪዎቻቸው ጉልበታቸው የሚበዘበዝ፣ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት የሚፈጸምባቸው፣ በረሃብ የሚሰቃዩ እና ሌሎችም በደሎች ይደርስባቸዋል።
ከእነዚህ መካከልም በተለይ ኦማን ውስጥ በሚገኙ አፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ሠርቷል።



