ሊዮኔል ሜሲ የነገሠበት የኳታር የዓለም ዋንጫ ዋና ዋና ክስተቶች
ሊዮኔል ሜሲ የነገሠበት የኳታር የዓለም ዋንጫ ዋና ዋና ክስተቶች
ከመነሻው ክስና ውዝግብ የገጠመው የኳታር የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅነት ድንቅ ክስተቶችን አስተናግዶ ሁሉን አጀብ ባሰኘ ሁኔታ ለፍጻሜ በቅቷል።
አርጀንቲናን ጨምሮ የዓለማችን ታላላቅ ቡድኖች ሽንፈት ሲገጥማቸው፣ ሞሮኮና ሌሎች ብዙም ትኩረት ያልተሰጣቸው ቡድኖች ደግሞ ታሪክ ሰርተዋል።
በመጨረሻም የ35 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ሊዮኔል ሜሲን የዋንጫ ባለቤት በማድረግ ደማቅ ታሪክ እንዲጽፍ ያስቻለው የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ሂደት ምን ይመስል ነበር?



