ብዝሃ ሕይወት ምንድን ነው? ጠቀሜታውስ?
ብዝሃ ሕይወት ምንድን ነው? ጠቀሜታውስ?
ብዝሃ ሕይወት በሰፊዋ ምድራችን ላይ በተለያዩ የተፈጥሮ አካባቢዎች የሚገኙ ማንኛቸውንም ፍጥረታት ያካትታል።
እነዚህም እንስሳት እና እጽዋት የመጠጥ ውሃ፣ ምግብ እና መድኃኒትን ጨምሮ ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ያቀርባሉ።
ከእዚህም ባለፈ በአግባቡ ከተያዙ የዓለማችን ዋነኛ ስጋት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልም የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
በተቃራኒው ደግሞ የምድራችን ብዝሃ ሕይወት ሃብት መመናመን ወይም መጥፋት የተፈጥሮን ሥርዓት በማዛባት የሰውን ልጅ ኑሮ በእጅጉ እንዲመሰቃቀል ያደርጋል።



