ሦስት ልጆቻቸው ዐይነ ስውር ከመሆናቸው በፊት ዓለምን እየዞሩ ያሉት ቤተሰቦች
ሦስት ልጆቻቸው ዐይነ ስውር ከመሆናቸው በፊት ዓለምን እየዞሩ ያሉት ቤተሰቦች
የኢዲት እና የሴባስቲያን ልጆች አንድ ቀን አይነ ስውር ይሆናሉ። ከአራት ልጆቻቸው ሦስቱ በዘር የሚተላለፍ እና በሂደት የዐይን ብርሃንን የሚያሳጣ በሽታ ተገኝቶባቸዋል።
በመሆኑም ወላጆች ችግሩ ከመከሰቱ በፊት በልጆቻው ላይ ትውስታ ለማስቀመጥ በርካታ የዓለም ክፍልን በመዘዋወር ለማሳየት ወስነዋል።
በሽታው ምንም አይነት ምልክት አይታይበትም። ሰዎች ከውልደታቸው ጀምሮ ይዘውት የሚመጡት ነገር ነው።
ይህ ችግር በልጆቻቸው ላይ እንደተከሰተ ያወቁት እነዚህ ካናዳውያን ቤተሰቦች የአንድ ዓመት ጉዞ ማድረግ ከጀመሩ ስድስት ወር ሆኗቸዋል።
በስድስት ወር ጊዜ ውስጥም በሦስት አህጉራት ስድስት አገራትን ጎብኝተዋል።



