በጦርነት መካከል ባዶ ቤት ተቆልፎባቸው ብቻቸውን የተተዉት የቤት ሠራተኞች በሊባኖስ
በጦርነት መካከል ባዶ ቤት ተቆልፎባቸው ብቻቸውን የተተዉት የቤት ሠራተኞች በሊባኖስ
የእስራኤል ጦር መዲናዋን ቤይሩትን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሚያካሂደው የአየር ድብደባ ምክንያት አንዳንዶቹ አሠሪዎች ነፍሳቸውን ለማትረፈወ ሲሸሹ የቤት ሠራተኞቻቸው ላይ ቤታቸውን ቆልፈው እንደሄዱ ነው።
ቀሪዎቹ ደግሞ ገንዘባቸውም ሆነ የጉዞ ሰነዶቻቸው በአሠሪዎቻቸው እጅ በመሆኑ መሄጃ አጥተው በጦርነቱ መካከል እየተንከራተቱ ነው።
በሰላሙ ጊዜም ቢሆን በከባድ ፈተና ውስጥ የቆዩት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ በሊባኖስ ውስጥ የሚገኙ የቤት ሠራተኞች አሁን በጦርነቱ ምክንያት የበለጠ ለችግር መጋላጣቸውን እየተናገሩ ነው።



