ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ቡና ለጤና እና ለዓለም ሥልጣኔ ስላበረከተው አስተዋጽኦ በጥቂቱ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ቡና ለጤና እና ለዓለም ሥልጣኔ ስላበረከተው አስተዋጽኦ በጥቂቱ

በዓለም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በየዕለቱ ቡና ይጠጣሉ። ቡና ቢያንስ ላለፉት 1500 ዓመታት እንደተጠጣ ይነገራል።

ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ይህ ፍሬ ዛሬ ዓለም ላለችበት ዕድገትም የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል በማለት ምሁራን ይጠቅሱታል።

በሌላ በኩል በሰውነታችን ውስጥ የተለያዩ በሽታዎችን በመከላከልና አዕምሮን በማንቃት አስተዋጽኦ እንዳለው የጤና ሙያተኞች ይመሰክራሉ።

ቢቢሲ በዚህ ቪዲዮ ስለቡና ታሪካዊ ዳራ፣ ጠቀሜታዎች እና የጎንዮሽ ጉዳቶች በአጭሩ አቅርቧል።