'ሕይወት ቀያሪ' የተባለው ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው ተሽከርካሪ ወንበር
'ሕይወት ቀያሪ' የተባለው ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው ተሽከርካሪ ወንበር
በመላው ዓለም 70 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ተሽከርካሪ ወንበር ያስፈልጋቸዋል። ነገር ግን ይህንን ዕድል የሚያገኙት 15 በመቶ የማይበልጡት ናቸው።
አይሜ በልጅነቷ በደረሰባት አደጋ እጆቿን እና እግሯን አጥታለች። ቢሆንም ግን ተስፋ አልቆረጠችም። የዘመኑን ቴክኖሎጂ ተጠቅማ መንገድ በሌለበት ቦታ ሁሉ መሄድ የሚችል ባለ ሰንሰለት ተሽከርካሪ ወንበር ሰርታለች።
ከራሷ አልፋም በመላው ዓለም ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ለመርዳት እየጣረች ነው።



