በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ትልቁ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሚገነባባት አረብ አገር
በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ትልቁ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሚገነባባት አረብ አገር
ለበርካታ አስርት ዓመታት በርካታ ኢትዮጵያውያን ለሥራ እና ለንግድ ሲስተናገዱባት የቆየችው ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ለቤተክርስቲያን መገንቢያ ሰፊ ቦታን ሰጥታለች።
በርካታ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች በሚኖሩባት ኤምሬትስ የእምነት ሥርዓታቸውን ለማከናወን የራሳቸው የሆነ ስፍራ ያልበራቸው ኢትዮጵያውያን፣ በአንድ ላይ ለመሰባሰብ እና በዓላትን በጋራ ለማክበር የሚያስችላቸው ቦታ ማግኘታቸውን ይናጋረሉ።
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በፋርስ ባሕረ ሰላጤዋ አቡ ዳቢ ትልቅ ቤተክርስቲያን ለመገንባት ጥረት እያደረጉ ነው። የቢቢሲ ዘጋቢዎች በቅርቡ ወደ ኤምሬትስ ባቀኑበት ጊዜ ስፍራውን ጎብኝተው ነበር።



