ህልሜ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ጥቁር ሕዝቦች ባሉበት ሁሉ ማዳረስ ነው፡ ቶማስ ጎበና
ህልሜ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ጥቁር ሕዝቦች ባሉበት ሁሉ ማዳረስ ነው፡ ቶማስ ጎበና
ቶማስ ጎበና ወይንም በመድረክ ስሙ ቶሚ ቲ ከተለያዩ የሙዚቃ ባንዶች ጋር በመሆን በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በመዘዋወር ሙዚቃ ተጫውቷል።
በተጨማሪም የቤዝ ጊታር ተጫዋቹ ቶማስ ከጥላሁን ገሠሠ፣ መሐሙድ አሕመድ፣ እጅጋየሁ ሽባባሁ (ጂጂ) እንዲሁም ሌሎች ታዋቂ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ጋር ሠርቷል።
በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ የተመሠረተው እና ጎጎል ቦርዴሎ ባንድ አባል የሆነው ቶማስ የዩኒሴፍ የበጎ ፈቃድ አምባሳደርም ነው።
ቶማስ በዩኒሴፍ አምባሳደርነቱ ሙዚቃን በኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣቶችን ለማነሳሳት እና ለማስተማር ይጠቀምበታል። አሁን ደግሞ ከድምጻዊት ሃሌሉያ ተክለጻድቅ ጋር በመሆን 'ውዴ' የተሰኘ የሙዚቃ ሥራውን ለአድምጫች አቅርቧል።



