ፕሮ. መረራ፡ የኬንያ ምርጫ በአፍሪካ ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል የሚል እምነት አሳድሮብኛል
ፕሮ. መረራ፡ የኬንያ ምርጫ በአፍሪካ ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል የሚል እምነት አሳድሮብኛል
የኬንያን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመታዘብ በአገሪቱ የሚገኙት ጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ምርጫው በአፍሪካ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል የሚል እምነት እንዲያድርባቸው እንዳደረገ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከቢቢሲ ጋር ናይሮቢ ውስጥ በነበራቸው አጭር ቆይታ በኬንያ ስለታዘቡት ምርጫ ያላቸውን ምልከታ ከኢትዮጵያ ጋር እያነጻጸሩ እንዲሁም ስለአገራቸው ወቅታዊ ሁኔታ ጠይቀናቸዋል።
ጠንካራ ፉክክር እያስተናገደ የሚገኘውን የኬንያን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመታዘብ የቀድሞው የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ይገኛሉ።



