በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከድቁና እስከ ቅስና የዘለቀው ፊሊፒንሳዊ ቤተሰብ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከድቁና እስከ ቅስና የዘለቀው ፊሊፒንሳዊ ቤተሰብ
ፊሊፒንስ ውስጥ ተወልደው ያደጉት ቀሲስ ዳንቴ አሎንዞ በ16 ዓመታቸው ነበር ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ካናዳ የተሰደዱት።
በአንድ ወቅት መጸሐፍ ቅዱስ ሲያነቡ ስለ ኢትዮጵያ ማወቃቸውን እና ካናዳ ወደ ሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አምርተው ባዩት ነገር በእጅጉ እንደተማረኩ ይገልጻሉ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላም የካቶሊክ እምነታቸውን ቀይረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትን ተቀበሉ። ከብዙ አገልግሎት እና ትጋት በኋላ ደግሞ ድቁና እና ቀስናን ተቀብለዋል።
ከእሳቸው በተጨማሪም ልጃቸው ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግል በስዕለት ሰጡ። ልጃቸው ዲያቆን ዮሐንስ አሎንዞ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፣ ስለ አገልግሎቱ እና ስለአባቱ ምን ይላል? ይህ ቪዲዮ ምላሽ አለው።



