በአፍሪካ የጨቅላ ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ ያግዛል የተባለውን የመተንፈሻ መሳሪያ የሠራው ነርስ

በአፍሪካ የጨቅላ ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ ያግዛል የተባለውን የመተንፈሻ መሳሪያ የሠራው ነርስ

ታንዛኒያ ውስጥ 26 በመቶ የሚሆኑ ያለ ጊዜያቸው የተወለዱ ሕጻናት የሚሞቱት ከመተንፈስ ጋር በተገናኘ ችግር ነው። በሌሎች የአፍሪካ አገራትም በተመሳሳይ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጨቅላዎች ለሞት ይዳረጋሉ።

እንዲህ ያለው ችግር የገጠማቸው ጨቅላዎች ሰው ሠራሽ የመተንፈሻ አጋዥ መሳሪያን ካገኙ ሕይወታቸውን ማትረፍ የሚቻልበት ዕድል አለ። ነገር ግን በበርካታ ከከተሞች ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ባሉ የጤና ተቋማት ውስጥ ይህ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ አይገኝም።

ይህ የጨቅላ ሕጻናትን ሕይወት ለመታደግ የሚያገለግለው መሳሪያ በ5 ሺህ ዶላር የሚገዛ ሲሆን ቢሆንም፣ በገጠር የጤና ተቋማት ውስጥ ባለመገኘቱ ጨቅላዎች ለስቃይ እና ለሞት ሲዳረጉ ቆይተዋል።

ይህንን የተመለከተው ታንዛኒያዊው ነርስ ዊልሰን ፉንጋሜዛ ይህንን መሣሪያ የሚተካ ፈጠራ ሠርቷል። ይህ የጨቅላ ሕጻናት የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያው በቀላሉ ከሚገኙ ግብዓቶች የተሠራ ነው።