“ልጆቼ የት ነው ያላችሁት?” ከፍርስራሽ ስር ልጆቻቸውን የሚፈልጉ አባት
“ልጆቼ የት ነው ያላችሁት?” ከፍርስራሽ ስር ልጆቻቸውን የሚፈልጉ አባት
ተፈጥሯዊ አደጋ የሆነው የመሬት መንቀጥቀጥ የጥንካሬ መጠን በሚለካበት የሬክተር ስኬል መሠረት በተከታታይ ቱርክ እና ሶሪያን ክፉኛ ያናወጣቸው ርዕደ መሬት ከባድ ከሚባሉት ውስጥ የሚመደቡ ናቸው።
በአደጋው በተለይ በርካታ የቱርክ አካባቢዎች ወድመዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሕንጻዎች በመፈራረሳቸው በአደጋው ጊዜ ቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ለሞት እና በፍርስራሾች ውስጥ ለመቀበር ተዳርገዋል።
ከዕለት ዕለት የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ሄዶ አሁን ከ20 ሺህ በላይ የደረሰው አደጋ አምስት ቀናት ቢሆነውም፣ በፍርስራሽ ውስጥ ተቀብረው በሕይወት ሊኖሩ ይችላሉ የተባሉ ሰዎችን ለማግኘት የሚደረገው ፍለጋ አልተቋረጠም።



