“ወደ አገሬ ከተመለስኩ ባሌ ይገድለኛል”

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የባሏን ድብደባ ለማምለጥ የተሰደደችው ፓሪሳ
“ወደ አገሬ ከተመለስኩ ባሌ ይገድለኛል”

ፓሪሳ በባሏ የሚደርስባትን ድብደባ ለማምለጥ ወደ ቱርክ ተሰድዳለች። በመሰደዷ ሊገድላት እየዛተባት ነው። ቢሆንም ግን አሁንም ወደ አገሯ የመባረር አደጋ ተጋርጦባታል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት በኢራን 'የክብር ግድያ' ጨምሯል። የክብር ግድያ ማለት በወንድ ዘመድ ሴቶች ላይ የሚፈጸም ነው።

ቤተሰብን አዋራዳችኋል በሚል የሚፈጸም ግድያ ነው። ወደ አገሯ ከተመለሰች ፓሪሳም ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል።