ሽመልስ አራርሶ እና ታዋቂው የኬንያ ዘም መሽሩምስ ባንድ ሲታወሱ

ሽመልስ አራርሶ እና ታዋቂው የኬንያ ዘም መሽሩምስ ባንድ ሲታወሱ

ታዋቂው ሙዚቀኛ ሽመልስ አራርሶ እና የኬንያው ዘም መሽሩምስ ባንድ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1980ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ አስከ ሽመልስ ህልፈት ድረስ ኬንያን እና ኢትዮጵያን በሙዚቃ ያስተሳሰረ የጋራ ታሪኮች አሏቸው።

ሽመልስ ከዘም መሽሩምስ ባንድ ጋር ሁለት አልበሞችን ሰርቷል። በሽመልስ ምክንያት ዘም መሽሩምስ ባንድ ወደ ኢትዮጵያ እየተመላለሰ ብዙ የሙዚቃ ድግሶችን አቅርቧል።

አምስት አስርት ዓመታት ያስቆጠረ ዕድሜ ያለው ከዘም መሽሩምስ ባንድ አባላት ከሆኑት አምስት ወንድማማቾች መካከል ሁለቱ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በዚህ ቆይታቸው ስለሽመልስ አራርሶ እና ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ስላቀረቧቸው የሙዚቃዎች ድግሶች አውግተውናል።

* ቪዲዮ፡ ፋሲካው መንበሩ

*ፕሮዲዩሰር፡ ኤልያስ ሙሉጌታ