በሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ሠራዊት ያሰማሩት አገራት እነማን ናቸው?
በሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ሠራዊት ያሰማሩት አገራት እነማን ናቸው?
አምስት የአፍሪካ ቀንድ እና የምሥራቅ አፍሪካ አገራት በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር ሠራዊታቸውን በሰማሊያ አሰማርተዋል።
እነዚህ የአገራት ሠራዊቶች ከአል ቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያለውን ጽንፈኛ ቡድን አልሻባብን በመቆጣጥር እና የሶማሊያን መንግሥትን በመደገፍ በአገሪቱ ውስጥ ቆይተዋል።
ሦስተኛው ዙር የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ በሚል ስያሜ ከመጪው ጥር ጀምሮ በሚሰማሩት የአገራት ወታደሮች ውስጥ በሶማሊያ ውስጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደማይሳተፉ እየተነገረ ነው። በአሁኑ ጊዜ በሶማሊያ የትኞቹ አገራት ወታደሮች አሏቸው?



