ኢራን በተለያዩ ጦርነቶች ውስጥ ከፊት እና ከጀርባ የምትሳተፍባቸው አምስት ምክንያቶች

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
ኢራን በተለያዩ ጦርነቶች ውስጥ ከፊት እና ከጀርባ የምትሳተፍባቸው አምስት ምክንያቶች

ምዕራባውያን ኢራን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሚደረጉ ጦርነቶች ውስጥ ከመንግሥታት እና ከታጣቂዎች ጀርባ አንዳንዴም ፊት ለፊት አለች እያሉ ይከሷታል።

በተለይ በተፋፋመው የመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት የኢራን ስም ጎልቶ ይነሳል። በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት፣ ሁለት ዓመት በሆነው በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት እንዲሁም በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት የኢራን እጅ በተዘዋዋሪ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ይባላል።

ይህም ኢራን በተለይ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ያለችበትን አስርታት የዘለቀ ፍጥጫን ተከትሎ ሊመጣብኝ ይችላል የምትለውን ጦርነትን ከርቀት የመከላከል ስትራቴጂዋ ነው ይባላል።

እዚህ ጥንታዊቷ አገር ኢራን በብዙ ጦርነቶች የምትሳተፍባቸውን አበይት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?