ለ35 ዓመታት ከወንዝ ውስጥ ብረታ ብረት በመሰብሰብ የኖሩት ‘ማግኔቱ’ አዛውንት
ለ35 ዓመታት ከወንዝ ውስጥ ብረታ ብረት በመሰብሰብ የኖሩት ‘ማግኔቱ’ አዛውንት
እኚህ ግለሰብ ጋንጉሊ ሳርካር ይባላል። ነዋሪነቱ በባንግላዲሽ መዲና ዳካ ነው። ላለፉት 35 ዓመታት ኑሯቸውን የመሩት ከሌሎች ሰዎች ለየት ባለ መልኩ ነው።
ከተማዋቸውን የሚያልፍ ቡሪጋንጋ የሚባል ወንዝ አለ። ሰው ሁሉ ከእዚህ ወንዝ ዓሳ በማጥመድ ኑሮውን ይደጉማል።
ጋንጉሊ ግን ላለፉት 35 ዓመታት ዓሳ አጥምደው አያውቁም። መተዳደሪያቸው ወንዙ ውስጥ የተጣሉ ብረታ ብረቶችን በማግኔት በመሰብሰብ ነው።
በቀን ከ10 እስከ 15 ኪሎ ግራም ብረት እየሰበሰቡ በመሸጥ ዘመናትን አሳልፈዋል፤ አሁን ግን ችግር ገጥሟቸዋል።



